image
image
image
image
image

በ2016 በጀት አመት በትምህርት ለትውልድ ስራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የክፍለ ከተማ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እውቅና ተሰጠ ።

ጥር 10, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በፕሮግራሙ ተገኝተው እንደተናገሩት ትምህርት የትውልድ ግንባታ ስራችን በመሆኑ ተማሪዎቻችን በስነ ምግባር በዕውቀትና በክሕሎት የሚገነቡባቸው ሲሆኑ በክ/ከተማችን ያሉ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎች ተሰርቷል በማለት ገልፀዋል ። ወ/ሮ አበባ እሸቴ አያይዘው የትምህርት ስራ በመንግስት ብቻ የሚከወን ሳይሆን ሀሉም ባለድርሻ አካላትና ወላጆች እንዲሁም ህብረተሰቡ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ላይ ከበፊቱ በተሻለ አግባብ መንቀሳቀስ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አሰፋ ግርማ በትምህርት ለትውልድ ተሳታፊ የሆኑትን በማመስገን የተሻለ ተግባርና ውጤት የ 3ተኛ ዙር የትምህርት ለትውልድ ስራዎችን ንቅናቄ በማስጀመርና የትምህርት ደረጃ ፣ የተማሪዎች ውጤትና የስነ-ምግባር ማሻሻል ውጤታማ የሆነ ሲሆን ይህን ለማስቀጠል ባለድርሻ አካለትና የሚመለከተው ሁሉ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል በማለት ገልፀዋል። በመጨረሻም በትምህርት ለትውልድ የተሻለ አስተዋጽኦ ለነበራቸው አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች