image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የበጋ መዝጊያ እና የክረምት ማስጀመሪያ የመምህራን እና የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሄደ።

ሰኔ 30, 2017
በንቅናቄው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፈቃዱ፣ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ፣ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት ተጀምሯል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በማስ እስፖርቱ ላይ ተገኝተው እንደገለፁት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለጤናችን አይነተኛ ፋይዳ አለው ብለው ከክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በተጨማሪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ተማሪዎች ጤናማ እና ደስተኛ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። አቶ ጥላሁን አክለውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የተማሪዎች ፍቅርን ለማጠናከር የጎላ ፋይዳ እንዳላው በመጥቀስ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባህላችን አድርገን ልናዳብረው ይገባል ብለዋል። የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ ግርማ በበኩላቸው በክረምት በትምህርት ቤቶች ላይ የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚደረግ ገልፀው ለተሳታፊ ትምህርት ቤቶች የምስጋና ሰርተፊኬት አበርክተዋል። ይህ ንቅናቄ በ90 ቀናት ከተያዙ መርሃ ግብሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚተገበር ይሆናል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች