image
image
image
image

በዛሬው የሠኞ ማለዳ መርሃ ግብር "የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ምንነትና አስፈላጊነት" ዙሪያ ላይ ለጽ/ቤቱ አጠቃላይ ባለሙያዎች እና ሱፐርቫይዘሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጥቷል።

ግንቦት 25, 2017
ስልጠናው ከልደታ ክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ተዘጋጅቷል። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ትምህርትን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማስተሳሰር እንዲሁም በእውቀትና በክህሎት የተሻለ ባለሙያ ሆኖ ለመገኘት ራስን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው እንደ ትምህርት ሴክተር 5000 ሠዎች የኢትዮ ኮደርስ እንዲመዘገቡ የሚጠበቅ መሆኑንና እስከ አሁን ከ500 በላይ መመዝገባቸውንና እኛም እንደ ልደታ ትምህርት ጽ/ቤት ፈር ቀዳጅ በመሆን እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ በማጠናቀቅ አለም ዓቀፍ ሠርተፍኬቱን ልንይዝ ይገባል ብለዋል። የልደታ ክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገመቹ ጌታቸው በበኩላቸው ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ራሳችንን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተዋወቅና ማዋሃድ እንደሚያስፈልግ ገልጸው እ.አ.አ በ2026 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው ታቅዶ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን በተለይ ደግሞ እንደ ትምህርት ጽ/ቤት ዳታ ሳይንስን ጠንቅቆ መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ባለሙያ የሆኑት አቶ ሠይፈ የ5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ምንነትና አስፈላጊነት እንዲሁም አራቱን የስልጠና ኮርሶች ማለትም ዌብ ፕሮግራሚንግ፣ አንድሮይድ ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ በዝርዝር አስረድተዋል። በትምህርት ጽ/ቤት የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በተሠጠው ስልጠና መሠረት ሁላችንም አራቱንም ኮርሶች በመውሰድ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች