image
image
image
image
image

ለመንግስት እና ለግል ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን እና የት/አመራሮች በሃገር አቀፍ ደረጃ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የሙያ ፈቃድ አሠጣጥና እና እድሳት ምዘናን አስመልክቶ ኦረንቴሽን ተሠጠ።

ግንቦት 13, 2017
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ለተመዛኝ መምህራን፣ ር/መምህራን፣ ም/ር/መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ስለምዘና ምንነት፣ ለምዘናው የሚያስፈልግ ቅድመ ዝግጅት እንዲሁም ከተመዛኞች የሚጠበቅ ስነምግባር አስመልክቶ በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ ገለጻ አድርገዋል። ምዘናው በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄድ ሲሆን መምህራን በሚያስተምሩት የት/ዓይነት እና የትምህርት እርከን የጽሑፍ ፈተና ከ75%፣ ማህደረ ተግባር ከ25% የሚሰጥ መሆኑን፤ በተመሳሳይ ለተመዛኝ የት/ት አመራሮች የሚሰጠው ፈተና በአመራርነት ዙሪያ case study የጽሑፍ ፈተና ከ80%፣ ማህደረ ተግባር ከ20% የሚሰጥ መሆኑን አቶ ገዳ ገልጸዋል። በሙያ ፈቃድ ምዘና ላይ በአጠቃላይ በልደታ ክ/ከተማ 247 ተመዛኞች የሚመዘኑ ይሆናል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች