image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ቀጥታ (online) የሚፈተኑ ተማሪዎች በተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች ልምምድ አካሄዱ።

ግንቦት 21, 2017
የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ ከቡድን አስተባባሪዎች ጋር በመሆን ተማሪዎቹ ልምምድ በሚያደርጉባቸው የፈተና ጣቢያዎች በመገኘት ምልከታ አካሂደዋል። ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱ ተማሪዎች በዛሬው እለት ያካሄዱት የሙከራ ፈተና ለመደበኛው የፈተና መርሃ ግብር የተሻለ ልምድ የሚያገኙበት እንደሆነ አቶ አሠፋ ተናግረዋል። የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል Moc Exam በ3 የፈተና ጣቢያዎች ተማሪዎች በበይነ መረብ ልምምድ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ዋናው የበይነ መረብ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ 1ኛ ዙር ሰኔ 23፣ 24 እና 25 እንዲሁም 2ኛ ዙር ሰኔ 26፣27 እና 30 በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ በ1ኛ ዙር ሐምሌ 1፣ 2 እና 3 እንዲሁም 2ኛ ዙር ሐምሌ 4፣ 7 እና 8 እንደሚሰጥ ቀደም ሲል በወጣ ፕሮግራም መገለጹ ይታወቃል። በተያያዘ በወረቀት የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 23፣24 እና 25 እንዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሀምሌ 1፣ 2 እና 3/2017 ዓ.ም ፈተናው እንደሚሰጥ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች