image
image
image
image
image

10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የስፖርት ሊግ ውድድር የመክፈቻ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ስቴዲየም በዛሬው እለት በድምቀት ተጀምሯል።

መጋቢት 13, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ በመክፈቻ በተደረጉ ውድድሮች የመጀመሪያውን ድል አስመዝግቧል። ውድድሩ ከጠዋት ጀምሮ በተደረጉት ግጥሚያዎች በደመቀ ሽብርቅ የቀጠለ ሲሆን የልደታ ክፍለ ከተማ የመምህራን የወንዶች የገመድ ጉተታ ቡድን ተጋጣሚውን የየካ ክ/ከተማ ቡድን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። ስፖርታዊ ውድድሩ በአትሌቲክስ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በቼዝ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በእግር ኳስ፣ በእጅ ኳስ፣ በውሀ ዋና፣ በባህል ስፖርቶች፣ በገመድ ጉተታ እንዲሁም የፓራኦሎምፒክ የውድድር አይነቶች በተማሪዎች እና በመምህራን መካከል ከትምህርት ሰአት ውጭ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ክ/ከተማችንን ወክላችሁ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ለምትወዳደሩ መምህራንና ተማሪዎች በሙሉ መልካም ዕድል እንመኛለን!!!

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች