image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ሰኔ 10/2017 ዓ.ም በሚጀመረው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ላይ በፈታኝነት፣ በሱፐርቫይዘርነት እና በጣቢያ ኃላፊነት ለተመደቡ አካላት ከፈተናው ጋር ተያይዞ አጠቃላይ ግንዛቤ ተሰጠ።

ሰኔ 05, 2017
የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በንግግራቸው በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ላይ የተስተዋሉ ችግሮች መኖራቸውን ገልጸው ችግሮቹን እዚህ አቅርበን ብቻ የምናልፈው ሳይሆን በተለይ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው በገቡ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። አያይዘውም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በጥብቅ ዲሲፕሊን ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የተቀመጡ ግዴታዎችን መተግበር አስፈላጊና ግዴታም ጭምር ነው ብለዋል። የትምህርት ጽ/ቤት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በበኩላቸው ባለፉት ቀናት የ8ኛ ክፍል ፈተና በምናስፈትንበት ወቅት የተስተዋሉ ችግሮችን ጠቅሰው ይህ የሆነበት ዋናው ምክንያት ከጣቢያ ኃላፊ፣ ከሱፐርቫይዘር፣ ከፈታኝ መምህራን፣ ከተፈታኝ ተማሪዎች እንዲሁም ከጸጥታ አካላት የሚጠበቁ ኃላፊነቶችን በአግባቡ ባለመወጣት ምክንያት የተፈጠሩ ክፍተቶች ሲሆን እነዚህ ክፍተቶች በ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ላይ እንዳይደገሙ በየደረጃው የተቀመጡ ኃላፊነቶች ተግባራዊ በማድረግ ግዴታችንን መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል። የትምህርት ጽ/ቤት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አቡበከር አህመድ በተመሳሳይ በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ላይ የተስተዋሉ ችግሮች በ6ኛ ክፍል ፈተና ላይ በፍጹም እንዳይደገሙ ለማድረግ በክ/ከተማ ደረጃ ወጥ የሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል። በጽ/ቤቱ የፈተናዎች አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት አቶ ኑረዲን ሶማ በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን ያቀረቡ ሲሆን በተለይ ፖስታ አስተሻሸግ፣ የተማሪ መረጃ በጾታ በአግባቡ አለመለየት፣ በፖስታው ላይ የሚጻፉ መረጃዎች በአግባቡ እና በሚነበብ መልኩ አለመጻፍ፣ የተከለከሉ ነገሮች በመፈተኛ ጣቢያዎች ይዘው የተገኙ አካላት መኖር እና ሌሎችንም ጉዳዮች በዝርዝር ገልጸው ውይይት ተደርጓል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች