image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የማስፈጸሚያ ሰነድ ለወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ለአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ ለሱፐርቫይዘሮች እና ለክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች አስተዋወቀ።

ግንቦት 28, 2017
የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በንግግራቸው እንዳሉት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ፈተናው እስከሚጠናቀቅበት ቀን ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካል በኃላፊነትና በተጠያቂነት ስሜት ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ያሉ ሲሆን ባለፉት ዓመታት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ስናስፈትን በጥንካሬም፣ በክፍተትም የተገለጹ በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጸው በተለይ በክፍተት የተገለጹትን ሙሉ በሙሉ ለማስተካከል ሁላችንም ኃላፊነታችንን መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል። በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በበኩላቸው የ2017 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ፣ ክፍተቶችንና ስህተቶችን ለመቀነስ በዋናነት ደግሞ ተማሪዎች የተሻለ ዝግጅት አድርገው ፈተናውን እንዲፈተኑ ለማድረግ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው ፈተናው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሁላችንም በኃላፊነት መስራት ይኖርብናል ብለዋል። በጽ/ቤቱ የፈተናዎች አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት አቶ ኑረዲን ሶማ በ2016 ዓ.ም በተሠጠው ከተማ አቀፍ ፈተና ላይ በፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ በፈታኝ መምህራን፣ በሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም በአስፈታኝ ት/ቤቶች ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶች መኖሩን ገልፀው እነዚህ ስህተቶች በ2017 ዓ.ም እንዳይደገሙ ሁሉም በየደረጃው ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል። የ2017 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የማስፈጸሚያ ሰነዱንም አቅርበው ውይይት ተደርጓል። ማስፈጸሚያ ሰነዱ የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ የሱፐርቫይዘሮች፣ የፈታኝ መምህራን፣ የተፈታኝ ተማሪዎች እና የጸጥታ አካላት ተግባርና ኃላፊነት ላይ ትኩረት አድርጓል። የቴክኖሎጂና መረጃ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ መንግሥቱ ኦሳቦ በ12ቱ የመፈተኛ ጣቢያዎች በጣቢያ ኃላፊነት፣ በፈተና ክፍል ኃላፊነት፣ በምገባና ጤና አስተዳደር እና በሱፐርቫይዘርነት የተመደቡ አካላትን ገለጻ አድርገዋል። በ2017 ዓ.ም በልደታ ክ/ከተማ ከተማ አቀፍ ፈተና ላይ የ8ኛ ክፍል 3031 ተማሪዎች፣ የ6ኛ ክፍል 3664 ተማሪዎች በ12 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለፈተና የሚቀመጡ ይሆናል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች