image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ8ኛና የ6ኛ ክፍል ፈተናዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገለጸ።

ግንቦት 27, 2017
ጽ/ቤቱ ፈተናዎችን ስኬታማ ለማድረግ ከፈተና ኮማንድ ፖስት ጋር ውይይት አድርጓል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አሰፋ ግርማ እንደተናገሩት የ2017 በጀት ዓመት የ8ኛና የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎችን በጥሩ አፈጻጸም ለማከናወን የሚያስችሉ የዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸው በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥም ሆነ ከውጭ ሊከናወኑ የሚችሉ የፈተና ግድፈቶችን ከዚህ በፊት ከነበረን የስራ አፈጻጸም ተነስተን ችግሮች እንዳይፈጠሩ መስራት ይገባል ብለዋል። አቶ አሰፋ አክለውም የፈተናዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በፈተናው ወቅት የሚተገበሩ ህጎችን ማወቅና መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው በፈተናው ወቅት ችግሮች ሲስተዋሉ ለኮማንድ ፖስት ችግሩን በመግለጽ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ይገባል ብለዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በቀጣይ የሚሰጡ የ8ኛና የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎችን ውጤታማ ለማድረግ ለፈተና ኮማንድ ፖስቱ መገለጹ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንደሚያደርግ ገልጸው ከዚህ በፊት የታዩትን የፈተና አፈጻጸም ክፍተቶች ትምህርት በመውሰድ በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ በመተባበር መስራት ይገባል ብለዋል። የ8ኛ ክፍል ከሰኔ 3-4/2017 እንዲሁም ከሰኔ10-12 ደግሞ የ6ኛ ክፍል ፈተና እንደሚሰጥ በፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች