image
image
image
image

☘☘☘☘ በሠላም ተጠናቀቀ!! ☘☘☘☘

ሰኔ 04, 2017
በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በሁለቱም የትምህርት መርሃ ግብሮች በ12 የመፈተኛ ጣቢያዎች ከሠኔ 03 - 04/2017 ዓ.ም ለ2 ተከታታይ ቀናት ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው ከተማ አቀፍ ፈተና ፍጹም ሠላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቀቀ፡፡ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ቀጣይ ሳምንት ከሰኔ 10 - 12/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በተመሳሳይ በስኬት እንድናጠናቅቅ በየደረጃው የበኩላችንን እንወጣ በማለት አሳስበዋል። አያይዘውም ለሁሉም የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ መልካም ምኞታቸውን ተመኝተዋል፡፡ ተፈታኝ ተማሪዎችም ፈተናቸውን እንዳጠናቀቁ ዩኒፎርም፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫና የመሳሰሉ የመማሪያ ቁሳቁሶችን በመለገስ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ ፈተናችሁን ላጠናቀቃችሁ ተማሪዎቻችን በሙሉ መልካም የእረፍት ወራት ይሁንላችሁ!!! ~~~~~~~~~//~~~~~~~~~

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች