image
image
image
image

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን የስፖርት ሊግ ውድድር በድምቀት ተጠናቀቀ።

ሚያዚያ 4, 2017
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በተካሄደው የመምህራን እና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር በተለያዩ የውድድር ዘርፎች 1 ዋንጫ፣ 2 የወርቅ ሜዳሊያ፣ 2 የብር ሜዳሊያ እና 10 የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን በድል አጠናቋል። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ ባስመዘገብነው ድል መደሠታቸውን ገልጸው ከመክፈቻ ጀምሮ እስከ መዝጊያ ፕሮግራም ድረስ ለስኬት ስትለፉ ለነበራችሁ የትምህርት ፅህፈት ቤት ባለሙያዎች፣ የወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን እንዲሁም በተለያየ ዘርፍ ስትወዳደሩ ለነበራችሁ ተማሪዎች እና መምህራን በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች