image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር አካሄደ።

ግንቦት 18, 2017
የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ጽ/ቤት የማኔጅመንት አባላትና አጠቃላይ ሰራተኞች ተገኝተዋል። በጽ/ቤቱ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሒሳብና የተ/ሳይንስ ሱፐርቫይዘር የሆኑት አቶ አለምብርሃን አዳል በአጠቃላይ በአመራርነት ዘመናቸው ያካበቷቸዉን ልምዶች፣ የነበሩ ተግዳሮቶችና ስኬቶች አስመልክቶ እውቀታቸውን አካፍለዋል። አቶ አለምብርሃን ከመምህርነት ጀምሮ ያላቸውን ልምድ ያካፈሉ ሲሆን በተለይ በተለያዩ ዘርፎች ላይ አመራር ሆነው ባገለገሉባቸው ጊዜያት ማለትም የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የወረዳ ህዝብ ግንኙነት፣ የወረዳ ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ የክፍለ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የክ/ከተማ ህዝብ አደረጃጀት ኃላፊ እንዲሁም ለበርካታ አመታት በሶስት ክ/ከተሞች ማለትም በአቃቂ ቃሊቲ፣ በቦሌ እና በልደታ የክ/ከተማ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው በሰሩባቸው አመታት ችግሮች ሲያጋጥማቸው እንዴት እንደፈቱት እና ባሳለፏቸው አመታት የነበሩ ስኬቶችን በዝርዝር አቅርበዋል። በእውቀት ሽግግሩ ላይ የተገኙ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች አቶ አለምብርሃን ባቀረቡት ልምድ በጣም መደሰታቸውን ገልጸው በተለይ የአመራርነት ጥበባቸውን፣ ከሰዎች ጋር ያላቸውን መልካም ግንኙነት፣ በተመደቡበት ማንኛውም ቦታ በቅንነት ተቀብለው መስራታቸውን፣ ችግሮችን የፈቱበት ችሎታቸውን እጅግ አድንቀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች