image
image
image
image
image

4 የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የኦን ላይን ምዝገባ የፈተና ቢጋሮችንና የማጠናከሪያ ትምህርት አሰጣጥን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

ታህሳስ 21, 2017
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አሰፋ ግርማ እንደተናገሩት ውይይቱ ትኩረት ያደረገው በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ኦለይን ምዝገባ ፣ ከ4ኛ_12ኛ እንዲሁም የ6ኛ 8ኛ ክፍል የፈተና ቢጋርን አስመልክቶ ነው ብለዋል። አቶ አሰፋ አክለውም ውይይቱ የማጠናከርያ ትምህርት አሰጣጥ እቅድ ዙርያ ም በክፍለ ከተማው ስር ለሚገኙ የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል ሲሉ ተናግዋል። በውይይቱም በ2016 ዓ.ም የነበሩ ክፍተቶችን በማረም በ2017 ዓ.ም ያለምንም ስህተት ምዝገባውን ለማከናወን የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል!! በ2017 ዓ.ም በልደታ ክፍለ ከተማ ከ7000 በላይ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ ይጠበቃልም ይጠበቃል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች