image
image
image
image
image

የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በልደታ ክ/ከተማ በ3 ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አደረገ።

ሚያዚያ 4, 2017
በኢፌዴሪ የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ የሆኑት ወ/ሮ ኡሪያ አሊ ባደረጉት ንግግር ድጋፉ ሴት ተማሪዎች ንፅህናቸው ተጠብቆ ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉና ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው ብለው ጤናማ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር መሰል ድጋፎችን ሚኒስቴሩ አጠናክሮ ይቀጥላሉ ሲሉም ገልፀዋል። ሴቶች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉና ውጤት እንዲያስመዘግቡ ምቹ ሁኔታ እየፈጠርን እንቀጥላለን ያሉት ሚኒስቴር ድኤታዋ የተለያዩ ተቋማትና በጎ አድራጊዎች የንፅህና መጠበቂያዎችን ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል። በንፅህና መጠበቂያ ምክንያት አንድም ሴት በትምህርቷ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳይደርስባት በትኩረት እንሰራለንም ሲሉ ወ/ሮ ኡሪያ ገልጸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች