image
image
image
image
image

በዛሬው መርሃ ግብር የ2018 በጀት ዓመት የተቋማት የልማት እቅድ አጠቃላይ ይዘቶች እና በእቅድ ውስጥ መካተት የሚገባቸውን ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ሰጠ። አስተዋውቋል።

ሰኔ 02, 2017
የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡ የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር አካሄደ። በዛሬው መርሃ ግብር የ2018 በጀት ዓመት የተቋማት የልማት እቅድ አጠቃላይ ይዘቶች ላይ ግንዛቤ ተሠጥቷል። ጽ/ቤቱ ለአጠቃላይ ሠራተኞች በእቅድ ውስጥ መካተት የሚገባቸውን ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች አስተዋውቋል። ቢጋሩን በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ አቡበከር አህመድ ያስተዋወቁ ሲሆን በልማት ዕቅዱ በአራቱ ዋና ዋና ክፍሎች መካተት የሚገባቸውን አበይት ጉዳዮች በዝርዝር አስረድተዋል። የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ ቢጋሩ የቀረበበት ዋናው ዓላማ በእቅዱ የተካተቱ አጠቃላይ ይዘቶችን በማወቅ በ2018 በጀት ዓመት እንደ ጽ/ቤት፣ እንደ ቡድን እና እንደ ዘርፍ ለሚዘጋጀው እቅድ የተሻለ ግንዛቤ ለማግኘት እንዲረዳን እና ለጽ/ቤቱ የተሠጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ተረድተነው ተግባራዊ እንድናደርግ ነው ብለዋል። የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በይዘቱ እና በዕቅድ አስተቃቀድ ዙሪያ ላነሷቸው በርካታ ጥያቄዎች የቡድን አስተባባሪዎች ምላሽ ተሰጥተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች