image
image
image
image
image

የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ተጀመረ።

ሰኔ 03, 2017
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቱ፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃፍቱ ብርሃኑ፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ዘሪሁን ሽፈርዳ፣ የኢትዮጵያ ተ.ወ.ማ ፕሬዚዳንት አቶ ሃሰን ሺፋ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ከትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ከአቶ አሠፋ ግርማ ጋር በመሆን በክፍለ ከተማው ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል በተስፋ ኮከብ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ፈተናውን በማስጀመር ተማሪዎችን አበረታተዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበባ እሸቱ ለ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ዓመቱን ሙሉ የደከሙበትን እና የለፉበትን ልፋት የሚያዩበትና ወደ ቀጣዩ የትምህርት እርከን የሚሸጋገሩበት በመሆኑ ተረጋግተው በመፈተን ውጤታማ መሆን እንደሚገባቸው በማመላከት መልካም ፈተና እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ሰላማዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ሂደቱን የሚከታተል የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ከማዋቀር አንስቶ በቂ የፈተና አስፈጻሚዎች ተመልምለው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመው የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸው ፈተናውን ለሚወስዱ ተማሪዎች በሙሉ መልካም ውጤት እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች