image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በሁለቱም መርሃ ግብር መስጠት ጀመረ።

ሚያዚያ 21, 2017
የሞዴል ፈተናው በክ/ከተማው ባሉ የመንግስት እና የግል የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚሰጥ ሲሆን በዋናነት በክልላዊና ከተማ አቀፍ ፈተና የተካተቱ የት/ዓይነቶች ላይ ትኩረት አድርጓል። የትምህርት ጽ/ቤት የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ እንዳሉት ይህ የሞዴል ፈተና በክ/ከተማ ደረጃ ለ2ኛ ግዜ የተሠጠ ሲሆን Table of Specification በማዘጋጀት፣ ፈተናውን ከሚያዘጋጁ መምህራን ጋር በመወያየት ተማሪዎቹን ለቀጣይ ፈተና ይበልጥ እንዲያዘጋጃቸው ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተ.ወ.ማ ፕሬዚዳንት አቶ ሃሠን ሺፋን ጨምሮ የጽ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች በየት/ቤቱ በመዘዋወር ጎብኝተዋል። ሞዴል ፈተናው ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚሠጥ ይሆናል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች