image
image
image
image
image

10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና የተማሪዎች የሳይንስና ፈጠራ አውደ ርዕይ "በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉህ ትውልድ ለሃገር ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት የመክፈቻ ፕሮግራም ተካሄደ።

ሚያዚያ 16, 2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት 10ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን እና የተማሪዎች የሳይንስና ፈጠራ አውደ ርዕይ "በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉህ ትውልድ ለሃገር ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት የመክፈቻ ፕሮግራም ተካሄደ። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በዛሬው የመክፈቻ ፕሮግራም የተመረጡ የሳይንስና ፈጠራ ስራዎችን እና በርካታ ትዕይንቶችን ያካተተ ደማቅ የሽብርቅ ትርዒቱን አቅርቧል። አውደ ርዕዩ እስከ ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 3 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች