image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ከ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ጋር የ3 ዓመት የስራ ውል ተፈራረመ።

መጋቢት 24, 2017
የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በንግግራቸው የ3 ዓመት የስራ ውል ስምምነቱን ማድረግ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት የምትሰሩትን ስራ በኃላፊነት እና በተጠያቂነት ጭምር እንድትሰሩ ለማድረግ እና በተለይ የ12ኛ ክፍል ውጤት ከማሻሻል አንጻር ከምንግዜውም በበለጠ ከፍተኛውን ሚና እንድትወጡ ለማድረግ ነው ብለዋል። አያይዘውም የት/ቤቶችን የኢንስፔክሽን ደረጃ በግብዓት፣ በሂደት እና በውጤት አሁን ካሉበት አንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ የሚጠበቅ መሆኑንም አቶ አሠፋ ገልጸዋል። የስራ ውል ስምምነቱ የተማሪዎች ውጤት ማሻሻል፣ የአቋራጭ እና አርፋጅ ተማሪዎች ቁጥር መቀነስ እና የት/ቤቶች የኢንስፔክሽን ደረጃ ማሻሻል አካቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች