image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የማለዳ የእውቀት ሽግግር አካሄደ።

ሚያዚያ 21, 2017
በእውቀት ሽግግሩ ላይ የጽ/ቤቱ ቡድን መሪዎች፣ አስተባባሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። በእለቱ የእውቀት ሽግግር የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ አጠቃላይ ያላቸውን የስራ ልምድ አካፍለዋል። አቶ አሠፋ ለረጅም ዓመታት በአመራርነት በሰሩባቸው ዘርፎችና ጽ/ቤቶች የነበራቸውን የአመራርነት ልምድ ለጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ያካፈሉ ሲሆን በተለይ በትምህርት ጽ/ቤት ያለው የስራ ተነሳሽነት፣ አብሮና ተባብሮ መስራት፣ ባለሙያዎች ለውጤት የሚያሳዩት ትጋት እንዲሁም ውጤታማ መሆን ይበልጥ ለመስራት እንዳነሳሳቸው አያይዘው ገልጸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች