image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በሌተናል ኮሎኔል አብዲሳ አጋ ቅ/አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የቀዳማይ ልጅነት ህፃናትን በጨዋታ የማስተማር ስነ ዘዴ ላይ ትኩረት ያደረገ የልምድ ልውውጥ አካሄደ።

ግንቦት 28, 2017
የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ በልምድ ልውውጡ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ት/ቤቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሠጠውን ተልዕኮ በመቀበል ተግባራዊ ማድረጉን አመስግነው በየት/ቤቱ ተመሳሳይ ተግባራት ቢኖሩም አተገባበሩ ላይ ግን ልዩነቶች እንደሚኖሩ ጠቅሰው ዋናው የልምድ ልውውጡ ዓላማ ት/ቤቱ ባለው ግብዓት፣ ባለው የሠው ኃይል በተሻለ መልኩ ያከናወናቸውን ተግባራት በመውሰድ እንደየት/ቤታችሁ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲደረግና በቅ/አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ለማድረግ ነው ብለዋል። በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ በመክፈቻ ንግግራቸው ት/ቤቱ በክ/ከተማው ከሚገኙ 18 የመንግስት ቅ/አንደኛ ት/ቤቶች መካከል የተመረጠው የተሻለ ተሞክሮ እንዳለ ኮሚቴው ለይቶ በማቅረቡ ሲሆን ከ6ቱ ጭብጦች አንፃር የተከናወኑ ስራዎች፣ የምዘና ስርዓቱ፣ በአካቶ ትምህርት የሚማሩ ተማሪዎችን እንዴት እንደሚያግዙ እንዲሁም ወረዳው ት/ቤቱ እንዲለወጥ ያገዘበትን አግባብ ጭምር ልምዳቸውን እንዲያካፍሉን ለማድረግ ነው ብለዋል። የት/ቤቱ አስተባባሪ ወ/ሮ ሙሉነሽ ገ/ህይወት ት/ቤቱ የህዝብ በነበረበት ጊዜ የነበሩ በርካታ ችግሮች በተለይም የነበሩ የመሠረተ ልማት ችግሮች፣ የመብራት፣ የመጸዳጃ ቤት፣ የግብዓት ችግር የነበረ ቢሆንም ት/ቤቱ ወደ መንግስት ከዞረ በኋላ በአዲስ መልክ ተገንብቶ ችግሮች ተቀርፈው ተማሪዎች ምቹ በሆኑ የመማሪያ ክፍሎ፣ መጫወቻ ቦታ እንዲሁም በተሟላ ግብዓት እየተማሩ መሆኑን ገልጸዋል። ወ/ሮ ሙሉነሽ አያይዘው በት/ቤቱ የመርጃ መሣሪያ አዘገጃጀት፣ የብዝሃ ቋንቋ አተገባበር፣ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች፣ የድጋፍና ክትትል አግባቦች፣ ከጥበቃ ጀምሮ ሁሉም የት/ቤቱ ማህበረሰብ ያላቸውን አንድነትና አብሮነት እና ሌሎች ለተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ የተከናወኑ ተግባራትን አቅርበዋል። የወረዳ 3 ትምህርት ጽ/ቤት የት/ቤት መሻሻል ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው አሠፋ እንደ ወረዳ የተከናወኑ ስራዎችን በተለይ አዋኪ ጉዳዮችን የፈቱበት አግባብ፣ ለት/ቤቶች የሚደረጉ ክትትልና ድጋፎች፣ የተማሪ ውጤት እንዲሻሻል የተከናወኑ ስራዎች፣ በዓመቱ ውስጥ የነበሩ ስኬቶች እና ሌሎችም የተሠሩ ስራዎችን አቅርበዋል። በልምድ ልውውጡ ላይ የተገኙ አካላት የተሠሩ ስራዎችን እየተዘዋወሩ የጎበኙ ሲሆን በተመለከቷቸው ተግባራትም መደሠታቸውንና ያዩትን ተሞክሮ ወደ ት/ቤታቸው ወስደው እንደሚያሰፉ ገልጸዋል ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች