image
image
image
image

ሰኔ 03 እና ሰኔ 04/2017 ዓ.ም በሚሰጠው የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናን አስመልክቶ ከጸጥታ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ።

ሰኔ 02, 2017
በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ ባደረጉት ገለጻ በቅድመ ዝግጅት፣ በፈተናው ዕለት እንዲሁም ፈተናው ከተጠናቀቁ በኋላ በአጠቃላይ ከጸጥታ አካላት የሚጠበቁ ተግባራትን አብራርተዋል። የጸጥታ አካላት ፈተናው ከመጀመሩ አስቀድመው የመፈተኛ ክፍሎችን በጥንቃቄ መፈተሽ፣ ጥቁር ሰሌዳውና ግድግዳው በአግባቡ መጽዳቱን ማረጋገጥ፣ ተፈታኝ ተማሪዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በአግባቡ መፈተሽ፣ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው አለመግባታቸውን ማረጋገጥ እና ሌሎችም ጉዳዮችን አቶ ገዳ ገልጸዋል። አያይዘውም ለፈተና የሚመደቡ መኪናዎች ፈተናው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሙሉ በሙሉ ለፈተና አገልግሎት ብቻ የሚዉሉ መሆኑን ገልጸው የፈተና ኮሮጆዎች ከፖሊስ ጣቢያ ከንጋቱ 12 ሰዓት የሚንቀሳቀስ መሆኑንና የዕለቱ ፈተና ሲጠናቀቅም በፖሊስ ታጅቦ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሚጓጓዝ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ፈተናው በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ የጸጥታ አካላት ትልቁን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል። በመጨረሻም ከጸጥታ አካላት ለተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ እና በጽ/ቤቱ የቡድኖች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገዳ ሞሲሳ ምላሽ ሠጥተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች