image
image
image
image

ከሰኔ 03 - 04/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናን አስመልክቶ ከፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ ከርዕሳነ መምህራን እና ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር በአጠቃላይ በቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ የነበሩ ጥንካሬዎች እና የነበሩ ክፍተቶችን በጋራ ገመገመ።

ሰኔ 02, 2017
በግምገማው ላይ በ12ቱም የፈተና ጣቢያዎች ለፈታኝ መምህራን፣ ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለተፈታኝ ተማሪዎች፣ ለመጋቢ እናቶች፣ ለጸጥታ አካላት፣ ለጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ለጥበቃ አካላት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በየደረጃው ግንዛቤ መፈጠሩን፣ የመፈተኛ ክፍሎች ጽዱ እና ዝግጁ መሆኑን፣ የተፈታኝ ተማሪዎች ስም ዝርዝር በየመፈተኛ ክፍላቸው መለጠፉ በአጠቃላይ በቅድመ ዝግጅት መከናወን የሚገባቸው ተግባራት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች እና የፈተና ክፍል ኃላፊዎች ገልጸዋል። በተቀመጡ የኦረንቴሽን ቀናት የተወሰኑ ፈታኝ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች እና ተፈታኝ ተማሪዎች መቅረት እና መዘግየት ካጋጠሙ ክፍተቶች መካከል የተጠቀሱ ናቸው። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ እና ሁለቱ የጽ/ቤቱ አስተባባሪዎች በማጠቃለያ ንግግራቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በሁሉም ጣቢያዎች መጠናቀቁና ለፈተና ዝግጁ መደረጉ መልካም መሆኑን ገልጸው በተለይ ታራሚ ተማሪዎች የሚፈተኑባቸው የፈተና ጣቢያዎች ላይ አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። አያይዘውም በት/ቤቶች ዙሪያ ያሉ አዋኪ ጉዳዮች ካሉ ለሚመለከታቸው በማሳወቅ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ማድረግ፣ ከምገባ ጋር ተያይዞ የወረደውን ሜኑ ተግባራዊ ማድረግ፣ የተፈታኝ ተማሪዎች የቁጥር መረጃ አስቀድሞ ዝግጁ ማድረግ፣ የፈተናው ዕለት ቀድሞ በፖሊስ ጣቢያ በመገኘት ፈተናውን መረከብ፣ በፈተናው ላይ የስራ ድርሻን የሚገልጽ ባጅ አድርጎ መገኘት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች