image
image
image
image
image

በውጤታማ አገልግሎት አሠጣጥ ተግባራት ዙሪያ ለወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች በ3ኛ ሩብ ዓመት የተደረገ ክትትልና ድጋፍ ግኝት የጋራ ተደረገ።

ግንቦት 19, 2017
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ የሪፎርም እና አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ፣ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት እና የእቅድና በጀት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ በመሆን ለወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች በውጤታማ አገልግሎት አሠጣጥ ተግባራት ዙሪያ ባደረጉት ክትትልና ድጋፍ ግኝት ላይ ከጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል። የክትትልና ድጋፍ ግኝቱን የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሱፐርቫይዘር የሆኑት አቶ ለይኩን ብርሃኑ ያቀረቡ ሲሆን በተደረገው ክትትልና ድጋፍ እያንዳንዱ ወረዳ የነበረውን ጥንካሬና ክፍተት እንዲሁም ያሉበትን ደረጃ [ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ] በሚል በዝርዝር አቅርበዋል። የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ ግርማ የቀረበውን ግብረ መልስ አስመልክቶ በተለይም በዝቅተኛ ደረጃ የተፈረጁ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች በእያንዳንዱ በቀረቡ ነጥቦች ላይ ራሳቸውን እንዲፈትሹ እና ጊዜ ሳይሰጡም እርምት እንዲወስዱ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። አቶ አሠፋ አያይዘውም በማጠቃለያ ምዕራፍ እንደ ክ/ከተማ ለሚካሄደው ክትትል፣ ድጋፍና ምዘና ከወዲሁ ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ ለጽ/ቤት ኃላፊዎቹ አሳስበዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች